Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከጣሊያን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጣሊያን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ፣ ከኤርትራና ከሶማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ኦስማን ሳላህና አብሽር ኦማር ጋር ተወያይተዋል፡፡

78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ “ሰላም፣ ብልጽግና፣ ለውጥና ዘላቂነት” በሚል መሪ ሀሳብ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ነው።

ሚኒስትሮቹ ከጉባኤው ጎን ለጎን በሀገራቱ ኢንቨስትመንት፣በንግድ፣በሰላምና በፀጥታ ትብብር እና ሽብርተኝነትን መከላከል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

ለዚህም ÷ሚኒስትሮቹ ከጉዳዩን ወደ ተግባር ለመቀየር እንዲቻል የጋራ መድረክ እንዲኖራቸው መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version