የሀገር ውስጥ ዜና

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሶዶ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Feven Bishaw

September 19, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሶዶ ወረዳ በአናቲ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ሰአት ላይ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ 49 ሰዎችን ጭኖ ከአዲስ አበባ እየመጣ ከሆሳዕና ወደ አዲስ አበባ ከሚጓዝ ላንድ ክሮዘር ተሸከርካሪ ጋር ሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመጋጨቱ የተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ4 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ከወረዳው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡