Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ወጣቱ የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፊታችን የሚከበሩት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ የወጣቱ ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

“የአብሮነት፣ የወንድማማችነትና የፍቅር መገለጫ የሆኑ ሐይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር” በሚል መሪ ሀሳብ ከ5ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች የተሳተፉበት ውይይት ተካሂዷል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በዓላቱ ያለምንም ፀጥታ እክል ኃይማኖታዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ለማስቻል ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዲችል ወጣቶች ትኩረት ሰጥተው በዝርዝር ውይይት ማድረጋቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ የአደባባይ በዓላት በሚከበሩበት ወቅት ልዩ ልዩ የጥፋት አጀንዳ ይዘው ሰርገውና ተመሳስለው የሚገቡ ኃይሎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ወጣቱ የከተማው ሰላም ባለቤት ሆኖ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ከመግባባት ላይ ተደርሷል።

Exit mobile version