አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘመናዊ ካሜራ አምራቹ ኦምኒቪዥን ኩባንያ እጅግ አነስተኛ መጠን ያላትን ካሜራ አስተዋውቋል።
ኩባንያው ‘የጨው ቅንጣት’ መጠን አላት የተባለችውን እና ለህክምና አገልግሎት የምትውለውን ካሜራ ነው ያስተዋወቀው።
ካሜራዋ ኦ.ቪ.ኤም 6948 የሚል ስያሜ የተሰጣት ሲሆን፥ ለእይታ የሚመችና ዘመናዊ ዲጂታል ምስል እንድታሳይ ተደርጋ የተሰራች መሆኗን ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል።
0 ነጥብ 65 ሚሊ ሜትር በ0 ነጥብ 65 ሚሊ ሜትር የምትለካው ካሜራዋ 1 ነጥብ 158 ሚሊ ሜትር የብርሃን ማስተላለፊያ አላት።
ካሜራዋ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ (ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ) ላይ እጅግ አነስተኛዋ ካሜራ ተብላ እውቅናም አግኝታለች።
ይህ የካሜራ ዓይነት ለተለያዩ የህክምና አገልግሎቶች በተለይም ለውስጥ የሰውነት ክፍሎች ለሚደረጉ ህክምናዎች ተመራጭ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
ምንም እንኳን ካሜራዋ ትንሽ ብትሆንም በሰው አካል ውስጥ ያሉ አንዳንድ ለማየት አስቸጋሪ ናቸው የተባሉ ምስሎችን በጥራት እንደምታነሳም ዘገባው አመላክቷል።
ለአጠቃቀም ምቹ መሆኗ የተነገረላት ካሜራ በአገልግሎት ወቅት የማትግል በመሆኑም ለህክምናው ዘርፍ ተፈላጊ መሆኗም ነው የተነገረው።
#camera #health #technologynews
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!