የሀገር ውስጥ ዜና

ኮርፖሬሽኑ ከማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ

By ዮሐንስ ደርበው

September 18, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ የማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልዑካን በማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማቋቋም ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ልምድ እንደሚወስዱ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ያለውን ልምድ በመጠቀም በማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት የሚያስችል እገዛ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል፡፡

በመድረኩ የማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን በትብበር ለመስራት መስማታቸውም ተጠቁሟል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በቆይታቸው የሃዋሳ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ መጎብኘታቸውንም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!