አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ተላላፊ በሽታዎችን ሳይከሰቱ ቀድሞ መለየትና መከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ መደረግ ጀመረ።
የፕሮጀክቱን ትግበራ አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመላ ሀገሪቱ የሚተገበረው ፕሮጀክቱ በ4 ሚሊየን ዩሮ ወጪ ለ5 ዓመታት ተግባራዊ እንደሚደረግና ማንኛውንም በሽታ በዘረመል ደረጃ ማወቅ እንደሚያስችል በውይይቱ ተገልጿል፡፡
የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ቶሌራ (ዶ/ር)÷ ከዚህ በፊት አዳዲስ በሽታዎች ሲከሰቱ ወደ ውጭ ሀገራት ተልከው የላቦራቶሪ ምርምራ ይካሄድ እንደ ነበር አስታውሰዋል፡፡
አሁን ላይ ግን ፕሮጀክቱ በሀገር ውስጥ የመስራት አቅምን ለመፍጠር እንደሚያግዝ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፕሮጀክቱ መንግስት በሽታን ለመከላከል በሀገሪቱ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘውን ፖሊሲ የሚደግፍ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!