አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም ነሐሴ ወር ውስጥ ለውጭ ገበያ ከቀረበ 27 ሺህ ቶን ቡና 140 ሚልየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በተያዘው በጀት ዓመት እስካሁን የኢትዮጵያ ቡና አቅርቦት 18 በመቶ መጨመሩን ገልጸዋል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት 350 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 1 ነጥብ 75 ቢልየን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን አስታውሰዋል፡፡
የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ከአርሶ አደሮች፣ ከባለድርሻ አካላት እና ክልሎች ጋር እየሰራን ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!