የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል 7 ነጥብ 4 ሚሊየን የመማሪያ መጽሐፍት እየተሰራጩ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

September 18, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ እየሩስ መንግሥቱ 10 ነጥብ 8 ሚሊየን መፅሐፍት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር መታተማቸውን ተናግረዋል፡፡

ከታተሙት መፅሐፍት መካከል 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ያህሉ እየተሰራጩ መሆናቸውን ጠቁመው÷ እስካሁን 1 ነጥብ 7 ሚሊየን መፅሐፍት ወረዳ ላይ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ተጨማሪ 3 ሚሊየን መፅሐፍትን ለማሳተም በጨረታ ሂደት ላይ መሆናቸውንም ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡

ታትመው በስርጭት ላይ ያሉ መፅሐፍት የ1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው÷ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መፅሐፍት በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት እንደሚታተሙ አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!