ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሶማሊያ ጦር 30 የአል ሸባብ ታጣቂዎች መደምሰሱን አስታወቀ

By Feven Bishaw

September 17, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ጦር ባካሄደው ዘመቻ 30 የአል ሸባብ ታጣቂዎች መደምሰሱን አስታወቀ።

ጦሩ በማዕከላዊ ሶማሊያ ባካሄደው ዘመቻ ታጣቂዎችን ጨምሮ ተሽከርካሪዎችን አውድሜያለሁ ማለቱን ሺንዋ ዘግቧል።

ጦሩ በማሃደይ እና መካከለኛው ሸበሌ አካባቢዎች ከፍተኛ የአል ሸባብ መሪዎችን ኢላማ ያደረገ ተጨማሪ ዘመቻ እያደረገ መሆኑን የሶማሊያ ማስታወቂያ፣ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል።

እስካሁን በተደረገው ዘመቻም ሙዱግ በተባለው አካባቢ በርካታ ስፍራዎችን ከታጣቂው ነጻ ማድረግ መቻሉንም አስታውቋል።

የአካባቢው ነዋሪዎችም የመንግስት የፀጥታ አካላትና የሃገሪቱ ጦር በርካታ አካባቢዎችን ነፃ ማድረጉን ተናግረዋል።