የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከኩባ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

September 16, 2023

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኩባ ፕሬዚዳንት ሚጉዌል ቤርሙዴዝ ጋር ተወያይተዋል።

የቡድን 77 እና ቻይና የመሪዎችና የመንግስታት ጉባዔ በኩባ ሀቫና ከተማ እየተካሄደ ነው።

አቶ ደመቀ÷ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከኩባው ፕሬዚዳንት ሚጉዌል ቤርሙዴዝ ጋር መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይታቸውም÷ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ ጉብኝቶችን ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን÷ ከኩባ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከኩባ ፓርላማ አፈ-ጉባዔ ጋርም በተለየዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!