የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

September 16, 2023

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ተሾመ÷ ከአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ተወካይ ም/ ሃላፊ ዴቪድ ክሪቫኔክ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ራሚዝ አልካባሮቭ እና በኢትዮጵያ የተመድ መልሶ ማቋቋምና ልማት ድርጅት አስተባባሪ ሳልህ ቱራን ጋር ነው የተወያዩት፡፡

በውይይታቸውም ÷ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን መርሐ ግብርን ለማሳለጥ በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የተቋማቱ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉ መናገራቸውን አምባሳደሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡