አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ኩባ ሃቫና ገብቷል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ኩባ ሲደርሱም በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀላፊዎችና እና በኩባ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
አቶ ደመቀ በኩባ ቆይታቸው የቡድን 77 የመሪዎች ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ጉባኤው በአሁኑ ወቅት የልማት ፈተናዎችን ለመወጣት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ሚና ላይ እንደሚመክር ተጠቁሟል።