የሀገር ውስጥ ዜና

በህዳሴ ግድቡ ቀጣይ የውሃ ሙሌት በግድቡ አናት ላይ ውሃ አይፈስም – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)

By Amele Demsew

September 14, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጣይ የውሃ ሙሌት ሂደት በግድቡ አናት ላይ የውሃ መፍሰስ እድል እንደሌለው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ባደረጉበት ጊዜ እንዳሉት÷ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሲቪል ግንባታ ስራ በጥሩ መንገድ በመፋጠኑ በቀጣይ በሚደረገው የውሃ ሙሌት ውሃው በግድቡ አናት ላይ የመፍሰስ እድል የለውም፡፡

ይህም የሆነበት ምክንያት የግድቡ ውሃ የመያዝ አቅም ከፍ በማለቱ እንደሆነ አስረድተዋል።

ሰሞኑን የግድቡ የውሃ ሙሌት በተበሰረበት ወቅት 4ኛውና የመጨረሻው መባሉ በቀጣይ ሙሌት ውሃ በግድቡ አናት ላይ እንደማይፈስ ለመግለጽ እንጂ ግድቡ መሞላት ያቆማል ማለት እንዳልሆነ ነው የገለጹት፡፡

የግድቡ የውሃ ሙሌት ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ በተያዘው ዕቅድ መሰረት እንደሚከናወንም አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ጳጉሜን 5 ቀን 2015 ዓ.ም ማብሰራቸው ይታወቃል።

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!