Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በድሬዳዋ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ 100 ሚሊየን ብር ቤተ መጻሕፍት ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ ከመደመር ትውልድ መፅሐፍ ሽያጭ በተገኘ 100 ሚሊየን ብር ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጧል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በወቅቱ እንዳሉት÷ የምንፈልጋትንና የበለፀገችውን ኢትዮጵያን ለመገንባት ትውልዱን በዕውቀት፣ በምክንያት እና በጥበብ ኮትኩቶ ማሳደግ ላይ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል።

የእውቀትና የጥበብ መቅሰሚያ ማዕከላትን በማስፋት ትውልድን በዕውቀት የማነጽ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡

ለዚህም ዘመናዊ የዕውቀትና የጥበብ መቅሰሚያ ማዕከላትንና ቤተ መጻሕፍት ን በስፋትና በጥራት መገንባት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቤተ መጻሕፍቱ መሰረት ድንጋይ የተቀመጠው በድሬዳዋ ማዕከላዊ ሥፍራ በ2 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በ100 ሚሊየን ብር ወጪ በዚህ ወር መገንባት የሚጀምረው ቤተ መጻሕፍት በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናል ተብሏል፡፡

የግል ባለሀብቶች እና ተቋማት ትውልድን በዕውቀት በሚያሻግሩ ልማቶች ላይ ሊሳተፉ እንደሚገባም መልዕክት መተላለፉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version