Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ630 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የ2016 ዓም አዲስ ዓመት በማስመልከት ለ630 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ ።

የክልሉ መንግስት በሰባት ማረሚያ ቤቶች በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ አግኝተው የፍርድ ጊዜያቸውን በመፈፀም ላይ ከሚገኙ የሕግ ታራሚዎች መካከል ለ630 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል።

በዚህም 618 ታራሚዎች መደበኛ ሙሉ ይቅርታ፣8ቱ በልዩ ይቅርታና 4 ታራሚዎች የእስራት ቅናሽ እንደተደረገላቸው ተመላክቷል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 16ቱ ሴቶች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትጵያ ክልል ከተመሠረተ በኋላ ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version