Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተዘጋጀ ብሔራዊ የጸሎት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተዘጋጀ ብሔራዊ የጸሎት መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል፡፡

የጸሎት መርሐ ግብሩ አዲሱን 2016 ዓመተ ምህረት በይቅርታና በእርቅ መቀበልን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመርሐ ግብሩ አዲሱ ዓመት የሀገር አንድነትና የሕዝቦች አብሮነት ይበልጥ የሚጸናበት እንዲሁም ለኢትዮጵያ የሰላምና የፍቅር ዓመት እንዲሆን ሁሉም ቤተ እምነቶች በጋራ ጸሎት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው የጳጉሜን ቀናትን የጸሎትና የንስሐ መርሐ ግብር በማውጣት የተለያዩ ቤተ እምነቶች ለሀገር ሰላምና አንድነት እንዲጸልዩ ማወጁ ይታወቃል።

በዛሬው ዕለትም የጸሎት መርሐ ግብሩ ማጠቃለያ የተካሄደ ሲሆን÷ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሃይማኖት አባቶችና የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version