የሀገር ውስጥ ዜና

በጎነት ከማይነጥፍ የመልካምነት እሴት የሚቀዳ እንዲሁ በነጻ የሚሰጥ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

By Amele Demsew

September 08, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎነት ከማይነጥፍ የመልካምነት እሴት የሚቀዳ እንዲሁ በነጻ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጳጉሜን 3 ቀን የበጎነት ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፥ በጎነት መስፈርት የለውም ብለዋል።

በጎነት ከማይነጥፍ የመልካምነት እሴት የሚቀዳ እንዲሁ በነጻ የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በበጎ ፈቃድ እያገለገላችሁ ያላችሁ ወጣቶችም ኢትዮጵያ የጸናች፣ የበለጸገችና ለአፍሪካ ኩራት እንድትሆን መሰረት እየጣላችሁ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።