Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፋር ክልል የበጎነት ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጎነት ቀን “በጎነት ለሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በአፋር ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ደረሳ መሐመድ እንዳሉት÷ ቀኑን የቢሮው ሰራተኞች ከደመወዛቸው ቀንሰው ሌሎችን እገዛ በማድረግ እያከበሩ ነው።

የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ መሐመድ አወል መኤ በበኩላቸው÷ በጎነት የሁልጊዜ ስራችን ሆኖ ሊቀጥል የሚገባ ተግባር ነው ብለዋል።

በዕለቱ በበጎ አድራጎት ስራ የተሠማሩ ማህበራት ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት የፖናል ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version