Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በ2024 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቡሩንዲ ጋር መስከረም 9 እና 15 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚያደርጋቸው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዝግጅት ለማድረግ ነው ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ የቀረበው፡፡

በዚሁ መሠረት በግብ ጠባቂነት÷ ታሪኳ በርገና፣ ቤተልሔም ዮሐንስ እና አበባ አጀቦ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡

እንዲሁም ለተከላካይ መስመር ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች÷ ብርቄ አማረ፣ ብዙአየሁ ታደሰ፣ ናርዶስ ጌትነት፣ ንጋት ጌታቸው፣ ቤተልሔም በቀለ፣ ነጻነት ፀጋዬ፣ ቅድስት ዘለቀ፣ መንደሪን ክንድይሁን እና ፀሐይነሽ ጁላ ናቸው፡፡

ለአማካይ ስፍራ ተጫዋጭነት ለጽዮን ፈየራ፣ ኒቦኒ የን፣ መሳይ ተመስገን፣ አረጋሽ ካልሳ እና ማዕድን ሳኅሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

ለአጥቂ መስመር ደግሞ ለሎዛ አበራ፣ ሰናፍ ዋኩማ፣ ረድዔት አስረሳኸኝ፣ ቱሪስት ለማ፣ ንግሥት በቀለ፣ አሬት ኦዶንግ፣ ማሕሌት ምትኩ፣ እሙሽ ዳንኤል እና አለሚቱ ድሪባ ጥሪ መቅረቡ ተገልጿል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ነገ ከ10፡00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ መተላለፉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version