Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ በአውቶብስና በከተማ ቀላል ባቡር ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጳጉሜን 1 የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ በከተማ አውቶብስና በከተማ ቀላል ባቡር ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ነው።

የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ መነሻቸውን ማዘጋጃ ቤት ያደረጉ 2 የጉዞ መስመሮች ላይ የነፃ ትራንስፖርት አገልግሎትን አስጀምረዋል፡፡

በዕለቱም የእንኳን አደረሳችሁ የምኞት መግለጫ ካርድና ለ20 እድለኞች የ6 ወር የነጻ የከተማ አውቶብስ ትኬት ማበርከታቸውን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

እየተሰጠ ያለውን ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት በየተርሚናሉ በመዘዋወር አገልጋዩ በሙያዊ ስነ ምግባር ሕብረተሰቡን ዘወትር እንዲያገለግል አቶ ምትኩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version