Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የክልሉን ግብርናና ቱሪዝም ዘርፎች በማልማት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉን የግብርናና የቱሪዝም ዘርፎች በማልማት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ርብርብ እንደሚደረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተርንና ሌሎች ተቋማት ዛሬ በዲላ ከተማ በይፋ ስራ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ የክልሉን የግብርናና የቱሪዝም ዘርፎችን በማልማት የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ ይደረጋል፡፡

በግብርና ልማት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የህዝብ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ጠቅሰው÷ ክልሉን የሰላምና ብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የህብረተሰቡን ተባባሪነት መታከል አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የክልሉ የውሃና ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር አክሊሉ አዳኝ በበኩላቸው ÷ክልሉ በገጠርና በግብርና ልማት የመበልጸግ ትልቅ ፀጋና አቅም ያለው መሆኑን ተናግረዋል ።

በተለይ ለግብርና፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ልማት ምቹ የሆነ መልክዓ ምድር፣ ለም መሬትና የውሃ ሃብትን ጨምሮ በርካታ ፀጋዎች መኖራቸውንም አንስተዋል።

Exit mobile version