Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ 1 ሺህ 107 የደምብ ማስከበር አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ “በፓራ ሚሊተሪ” የሰለጠኑ 1 ሺህ 107 የደምብ ማስከበር አባላትን አስመረቁ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ “በፓራ ሚሊተሪ” ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 107 የደምብ ማስከበር አባላትን አስመርቀን ወደ ስራ አስገብተናል ብለዋል፡፡

የደምብ ማስከበርን በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይል እና በአሰራር እንዲሁም በግብዓት እንዲጠናከር አድርገናልም ነው ያሉት።

ተመራቂዎች ወደስራ ሲገቡ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት፣ በታማኝነት እና በአገልጋይነት መንፈስ እንዲያከናውኑም ከንቲባዋ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Exit mobile version