Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት አመራር የማደራጀት ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት አመራር የማደራጀት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አባላት ዛሬ ከደብረብርሃን ከተማ እና ከሰሜን ሸዋ ዞን የአስተባባሪ አባላት ጋር በአመራር አደረጃጀትና መሰል ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር)÷ አዲሱ አመራር የህዝቡን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ በአጭር ጊዜም ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚነሳበትን ሁኔታ እንደሚፈጠር ተናግረዋል።

በክልል ደረጃ የተሰራው የአመራር ማደራጀት ስራ በዞንና በከተማ አስተዳደሮች የአስተባባሪ አባላትን በማደራጀት መቀጠሉን ገልጸው፤ በቀጣይም በአጭር ቀናት እስከ ቀበሌ ድረስ በተመሳሳይ መንግስታዊ መዋቅሩን የማጠናከር እና አመራር የማደራጀት ስራ ይሰራል ብለዋል ።

በአበበ የሸዋልዑል

Exit mobile version