አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015/16 የመኸር እርሻ ከ17 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት መታረሱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለስ መኮንን ÷ በ2015/16 የመኸር እርሻ እንዲሁም የበልግና የመስኖ የግብርና ሥራን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው÷ ከሌሎች ዓመታት በተለየ ዘንድሮ ከ17 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ መሬት መታረሱንም አስታውሰዋል።
ከዚህ ውስጥም ከ7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር በላይ እርሻ በኩታ ገጠም የለማ መሆኑን መግለጻቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።