Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምዕራብ ጎንደር ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 289 የቱርክ ሽጉጥ እና 2 ባለአንድ እግር ክላሽ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)መነሻውን መተማ ወረዳ ኮኪት ቀበሌ ያደረገው መኪና ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ ሲንቀሳቀስ ተያዘ።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪውን የያዘው አይሱዚ የጭነት መኪና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና ጥይት በመጫን በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገንዳዉኃ ከተማ መግቢያ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ መያዙን ከምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መሳሪያው በተሽከርካሪዉ የመጫኛ ወለል ስፖንዳ ላይ በተበየደ ተጨማሪ ስፖንዳ በውስጥ መያዙ ነው የተነገረው።

በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉት መሳሪያዎች 289 የቱርክ ሽጉጥ ፣ 2 ባለአንድ እግር ክላሽ፣ 4 ሺህ 337 የቱርክ ሽጉጥ ጥይት ፣185 የብሬን ጥይት ነው።

የተሽከርካሪው ሹፌርም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ታዉቋል።

Exit mobile version