የሀገር ውስጥ ዜና

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር በመሆን ተሾሙ

By Amele Demsew

August 31, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋን (ፕ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቋቋም በአዋጅ መጽደቁን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለዩኒቨርሲቲው ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪም አዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን ቦርዱም ዩኒቨርሲቲውን በሃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንቶችን በቀጣይነት እንደሚሾም የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡