አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 764 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ 10 ወንዶች እና አንድ ሴት ናቸው።
እድሜያቸው ከ18 እስከ 38 አመት መሆኑንም ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።
ከዚህ ውስጥ አምስቱ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ ሁለቱ ከትግራይ ክልል ለይቶ ማቆያ፣ ሶስት ሰዎች ከአፋር ክልል ለይቶ ማቆያ እንዲሁም አንድ ግለሰብ ከኦሮሚያ ክልል አዳማ ለይቶ ማቆያ መሆናቸው ተገልጿል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ አምስቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ ስድስቱ ደግሞ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው ተብሏል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ36 ሺህ 624 ሰዎች ምርመራ መደረጉም ተገልጿል።
አሁን ላይ 138 ሰዎች በህክምና ላይ ሲሆኑ፥ ስድስት ተጨማሪ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።
እስካሁንም 105 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ነው የተገለጸው።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።