የሀገር ውስጥ ዜና

ለጷጉሜን ቀናት የተሰጡ ስያሜዎች ይፋ ተደረጉ

By Amele Demsew

August 31, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የጷጉሜን ቀናት የሚከበርበትን እና ለእያንዳንዱ ቀናት የተሰጡ ስያሜዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም ፦ ጷጉሜ 1 የአገልግሎት ቀን ጷጉሜ 2 የመስዋዕትነት ቀን ጷጉሜ 3 የበጎነት ቀን ጷጉሜ 4 የአምራችነት ቀን ጷጉሜ 5 የትውልድ ቀን ጷጉሜ 6 የአብሮነት ቀን ተብለው ተሰይመዋል፡፡

የአብሮነት ቀን በተለየ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበርም አገልግሎቱ ገልጿል፡፡ በዙፋን ካሳሁን