አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የጷጉሜን ቀናት የሚከበርበትን እና ለእያንዳንዱ ቀናት የተሰጡ ስያሜዎችን ይፋ አድርጓል።
በዚህም ፦
ጷጉሜ 1 የአገልግሎት ቀን
ጷጉሜ 2 የመስዋዕትነት ቀን
ጷጉሜ 3 የበጎነት ቀን
ጷጉሜ 4 የአምራችነት ቀን
ጷጉሜ 5 የትውልድ ቀን
ጷጉሜ 6 የአብሮነት ቀን ተብለው ተሰይመዋል፡፡
የአብሮነት ቀን በተለየ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበርም አገልግሎቱ ገልጿል፡፡
በዙፋን ካሳሁን