የሀገር ውስጥ ዜና

ከሲንጋፖር የኢኮኖሚ ልማት ቦርድ አመራር ጋር ውይይት ተደረገ

By Mikias Ayele

August 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሚሽነር ሌሊሴ ነሚ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች  ኮርፖሬሽን ስራ አስፈጻሚ አክሊሱ ታደሰ ከሲንጋፖር የኢኮኖሚ ልማት ቦርድ አመራር ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

 

በውይይታቸውም÷ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች በኢንቨስትመንት  ዘርፉ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በሚያስችሉ የፖሊሲ ማሻሻዎች ላይ መምከራቸውን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡