Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በድሬደዋ ግማሽ ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬደዋ ከተማ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ሥራዎች በ494 ሚሊየን ብር ወጪ እየተከናወኑ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለፉት ዓመታት የተሰሩ የጎርፍ መከላከያ ግንቦችና በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞች ጎርፍን በመከላከል በኩል አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውም ተመላክቷል።

የድሬዳዋ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ አቶ ያሲን አሕመድ እንደገለጹት ÷ ባለፉት ዓመታት የተገነቡት የጎርፍ መከላከያ ግንቦች ችግሩን በከፍተኛ ሁኔታ ቀርፈውታል፡፡

እነዚህን ሥራዎች ለማጠናከርና ባለፈው የበልግ ዝናብ ወቅት በተከሰተ ጎርፍ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ሥራ በ494 ሚሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም ቀደም ሲል የተገነቡ የጎርፍ መከላከያ ግንቦች ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጡ የሚያግዙ ልማቶች በዋና ዋና የጎርፍ መውረጃዎች ላይ እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም በጎርፍ የተጎዱ ግንቦችንና መንገዶችን የመጠገን ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መንግስት ችግሩን ለመከላከል የገነባቸው ግንቦች መሠረታዊ ለውጥ እያመጡ መሆናቸውንና እየተካሄዱ ያሉ የልማት ሥራዎች ቀደም ሲል በጎርፍ አደጋ ሲደርሱ የነበሩ ችግሮችን የሚያስቀሩና የህዝብን ጥያቄዎች የሚፈቱ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር በ1998 ዓ.ም ተከስቶ የነበረው የጎርፍ አደጋ ለ256 ሰዎች ህይወት ማለፍ፣ ከ10 ሺህ በላይ ቤተሰቦች

Exit mobile version