የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

By Amele Demsew

August 29, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄደ፡፡

ዛሬ በተካሄደው የስራ ማስጀመሪያ መረሐ ግብር ላይ÷ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ወንድማማችነትና መፈቃቃድ ብዙ ርቀት ያስጉዘናል ብለዋል፡፡

ለሕዝቦች አንድነትና እኩል ተጠቃሚነት እንደሚሠሩም ተናግረዋል፡፡

ይህ ክልል እውን እንዲሆን ጠንካራ ትግልና ሕዝበ ውሳኔ ያደረገው ሕዝብም ምስጋና ይገባዋል ነው ያሉት፡፡

በማስተዋል አሰፋ

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!