Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 02፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)  የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ክቡር ሳልቫኪር ማያርዲት ጋር ትናንት ግንቦት 1 ቀን 2012 ዓም በጁባ ተገኝተው በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ።

አቶ ገዱ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክትም ለፕሬዝዳንት ሳልቫኪር አድርሰዋል።

በኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ውስጥ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉስልጣን አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ ተካተዋል።

በደቡብ ሱዳን ወገን የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ማይክ አይ ዴንግን ጨምሮ የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት ክብርት ቢአትሪስ ክሃምሲ ዋኒ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣን ተገኝተዋል።

Exit mobile version