Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዩሮ ለመገበያያነት ያለው አቅም እያሽቆለቆለ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩሮ በዓለም አቀፍ ገበያ ለመገበያያነት የመዋል አቅሙ በፈረንጆቹ ሐምሌ ወር ማሽቆልቆሉ ተሰምቷል፡፡

የዓለም አቀፍ ኢንተርባንክ ፋይናንሺያል ቴሌኮሙኒኬሽን ማኅበር (ስዊፍት) መረጃ እንዳመላከተው÷ በመገበያያነቱ የዓለማችን ሁለተኛ የሆነው ዩሮ በሐምሌ ወር በድንበር ተሻጋሪ ግብይቶች ወደ 24 ነጥብ 4 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡

ይህም ከሰኔ ወር ጋር ሲነፃፀር 6 ነጥብ 83 በመቶ ለመገበያያነት የመዋል አቅሙ መቀነሱ ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል የአሜሪካ ዶላር የመገበያያት አቅም ወደ 46 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ማለቱን ስዊፍትን ጠቅሶ አር ቲ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version