Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአማራ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

የቀድሞውን ርዕሰ መሥተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ የአቶ አረጋ ከበደን የርዕሰ መሥተዳድርነት ሹመት ያጸደቀው ምክር ቤቱ በአዲሱ ርዕሰ መሥተዳድር በእጩነት የቀረቡትን የተለያዩ ሹመቶች ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

ከሰሞኑ ወቅታዊውን የክልሉን የጸጥታ ችግር ከገመገሙ በኋላ የፈጻሚ አካሉን አደረጃጀት መቀየር እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ ፥ የእጩ ተሿሚዎችን ዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በዚህም፦

1. አቶ አብዱ ሁሴን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር

2. አህመዲን መሐመድ(ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

3. ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ

4. ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማእረግ የማሕበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

5. አቶ ደሳለኝ ጣሰው በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ

6. ጋሻው አወቀ(ዶ/ር) የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኃላፊ

7. አቶ ብርሃኑ ጎሽም የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ

8. መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

9. ስቡህ ገበያው(ዶ/ር) የአማራ ክልል ሥራ እና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ ክብረት አህመድ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

11. አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ

12. ደመቀ ቦሩ(ዶ/ር) የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ

ከዚህ ውጭ ያሉ ሌሎቹ ተቋማት ባሉበት እንደሚቀጥሉ ርዕሰ መሥተዳድሩ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version