አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎፋ ዞን መሎ ጋዳ ወረዳ ዚታ ቀበሌ አንዲት ፍየል ስድስት ግልገሎችን ወለደች፡፡
ከተወለዱት ግልገሎች መካከል ሦስቱ ሴት እና ሦስቱ ወንድ ግልገል ሲሆኑ÷ አንደኛዋ ግልገል ከተወለደች በሁለተኛው ቀን መሞቷ ተገልጿል፡፡
የቀሩት አምስቱ ግልገሎች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ከወረዳው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ፍየሏ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ የወለደች ሲሆን÷ በመጀመሪያ ሁለት መንታ ግልገሎችን እንዲሁም በሁለተኛው ሶስት ግልገሎችን መውለዷን የበጓ ባለቤት የሆኑት አርሶ አደር ተናግሯል፡፡
መሰል ክስተት አልፎ አልፎ እንደሚከሰት የገለፁት የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና የእንሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ተመስገን በዞኑ ግን የመጀመሪያ መሆኑን መናገራቸውን ከዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡