አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የአመራር ሽግሽግ በማድረግ አዳዲስ ሹመቶችን እና ምደባ አካሄደ።
2015 ባደረገው ግምገማ የተገኙ ውጤታማ ጥንካሬዎችንና ድክመቶችን መለየቱን አስተዳደሩ ገልጿል።
ከዚህም በመነሳት ጠንካራ ስራዎችን የበለጠ ለማላቅ ፣ የተቋማት ሪፎርምን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ብልሹ አሰራሮችን ለማረም ከከተማ እስከ ወረዳ 280 አመራሮችንና 5442 የመንግስት ሰራተኞችን ተጠያቂ ማድረጉን አስታውቋል።
በሌላ በኩል የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ የአመራር ሽግሽግ በማድረግ አዳዲስ ሹመቶችን እና ምደባም መስጠቱን ነው ያመለከተው።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ሲሳይ ጌታቸው ኦበራ – የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
2. ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ረዳ – በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
3. ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ ረታ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የምግብና መድሃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
4. ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ አህመድ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
5. አውራሪስ ከበደ በቀለ- የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
6. ዶ/ር ኢ/ር እሸታየሁ ክንፉ ተስፋዬ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የስትራቴጂክ ፕሮግራሞች ማኔጅመንት ጽ/ቤት ኃላፊ
7. አቶ በላይ ታደለ ዞዴ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ የፕሮጀክቶች ክትትል አማካሪ
8. አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ ፋልታሞ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ
9. አቶ ሞላ ንጉስ ፈንታቢል – በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአፈ ጉባኤ አማካሪ
10. አቶ ተክሌ ዲዶ ሙራስ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአፈጉባኤ የህግ አማካሪ
11. አቶ መላኩ ታምሩ ተሰማ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ በፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ
12. ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ መኮንን- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ
13. አቶ ከበደ ካሳ ማሞ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የስትራቴጂክ ስራ አመራር ዘርፍ አስተባባሪ
14. ዶ/ር ሚኤሳ ኤሌማ ሮቤ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የኮሙኒኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ
15. አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሄር አለማየሁ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የዴሞክራሲ ባህል ዘርፍ አስተባባሪ
16. ወ/ሮ ጸዳለች ሚካኤል አደም- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የሃብት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ
17. አቶ ዳርዳር ብርሃኑ ወልደአብ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የልዩ ፅ/ቤት ኃላፊ
18. አቶ ሚደቅሳ ከበደ ዳዲ- የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ
19. ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ ወርቂ- በትምህርት ቢሮ ስርዓተ ትምህርት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
20. አቶ ደስታ መርጋ ገረሱ- የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ ኃላፊ
21. አቶ ሞሊቶ አባይነህ ኢርካሎ- መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አገልግሎት ማሻሻል ዘርፍ ኃላፊ
22. አቶ ከድር አደም በዳሶ- የስትራቴጂክ ፕሮግራሞች ማኔጅመንት ጽ/ቤት አማካሪ
የክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች
1. ወ/ሮ አይዳ አወል- የአዲስከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
2. አቶ ታረቀኝ ገመቹ ያደታ- የለሚኩራ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
3. አቶ አበበ ተቀባ ምህረቱ- የአራዳ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. አቶ ወልዴ ወገሴ ናኦ- የጉለሌ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።