Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 16 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የአንድ ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2 ሺህ 383 የላብራቶሪ ምርመራ 16 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪም ህይወታቸው አልፏል።

ሚኒስቴሩ በፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው እለታዊ ሪፖርቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 13 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው  ሲሆኑ፥ ሁለቱ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው። አንድ ሰው ግን የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው ብሏል።

በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 210 መድረሱን አስታውቋል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 7 ወንድ እና 9 ሴት መሆናቸውን፤ እድሜያቸውም ከ20 እስከ 60 ዓመት መሆኑን አመልክቷል።

የመኖሪያ ቦታቸውም አዲስ አበባ የሆኑት 13 ሲሆኑ፥ 1 ሰው በአማራ ክልል በወልዲያ ለይቶ ማቆያ እና ሁለት ሰው በደቡብ ክልል በወላይታ ሶዶ እና ጉራጌ  ዞን ቡታጅራ  ከተማዎች የሚገኙ ናቸው።

Exit mobile version