አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የቁም እንስሳት የተገኘው ገቢ ከ2014 አንጻር በ11 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በተጨማሪም ከ2014 በጀት ዓመት አንጻር÷ በቁጥር የ46 ሺህ 378 እንስሳት ቅናሽ ማሳየቱን በሚኒስቴሩ የእንስሳትና እንስሳት ተዋጽዖ ግብይት ዴስክ አስተባባሪ አበበ ታደሰ ተናግረዋል፡፡
በተጠናቀቀው ዓመት ወደ ኦማን፣ የመን፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኩዌት እና ሊቢያ 89 ሺህ 338 የቁም እንስሳት ተልኮ 16 ነጥብ 75 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ነው ያስታወቁት፡፡
በዋናነት የቁም እንስሳት ኮንትሮባንድ መስፋፋት፣ የላኪዎች የፋይናንስ አቅም ውስን መሆን፣ የቁም እንስሳት ላኪዎች ከዘርፉ መውጣት፣ የትራንስፖርት ዕጥረት፣ የመጫኛ ዋጋ መወደድ እና የገበያ መዳረሻ አለመስፋፋት ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!