Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ደን ሽፋን 17 በመቶ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2021 ከሳተላይት የተወሰዱ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ በተከናወነ ሥራ በኢትዮጵያ ያለው የደን ሽፋን 17 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ደን ልማት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ደንን በአራት ባዮም ማለትም Acacia-Commiphora፣ Combretum-Terminalia፣ Moist Afromontane እና Dry Afromontane በመመደብ የደን ሽፋን መረጃ ማውጣት መቻሉን በኢትዮጵያ ደን ልማት የደን ሀብት ጥናት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ብስራት ኃ/ሚካኤል ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በኢትዮጵያ 19 ሚሊየን 295 ሺህ 696 ሔክታር መሬት በደን መሸፈኑን ነው ያስረዱት፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርም ለደን ሽፋን መጨመር፣ ለደን ሥነ-ምኅዳር መጎልበት፣ ለብዝኃ-ሕይወት መጨመር እና የካርበን ልቀትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው አብራርተዋል፡፡

የሀገሪቱ የደን ሽፋን መጠን በሁለት ወይም ሦስት ዓመት ጊዜ እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2013 የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 15 ነጥብ 5 በመቶ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.