አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚኒስትሮች ኮሚቴ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመግታት የሚያግዙ እና ተጨማሪ የአሰራር ማሻሻያ የሚጠይቁ ሁለት መመሪያዎችን ተወያይቶ ማፅደቁን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ 49 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው አንስተው፥ ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ቫይረሱ በፍጥነት የመዛመት ዕድል እንዳለው በግልፅ ያሳያል ብለዋል።