አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚኒስትሮች ኮሚቴ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመግታት የሚያግዙ እና ተጨማሪ የአሰራር ማሻሻያ የሚጠይቁ ሁለት መመሪያዎችን ተወያይቶ ማፅደቁን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ 49 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው አንስተው፥ ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ቫይረሱ በፍጥነት የመዛመት ዕድል እንዳለው በግልፅ ያሳያል ብለዋል።
የወረርሽኙ አዝማሚያ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት በወቅታዊ ጉዳዮች ሳንዘናጋ የጥንቃቄ መመሪያዎችን አጥብቀን ተግባራዊ እናድርግ ሲሉም አሳስበዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።