የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

By Amele Demsew

August 19, 2023

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ጉባኤ በዛሬ ውሎው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እና የአፈ ጉባኤ ሹመትን አጽድቋል፡፡

በዚህ መሰረትም÷አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በምክር ቤቱ ተሹመዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ ቃለ መሃላቸውን በፈጸሙበት ጊዜ እንደገለጹት÷በቀጣይ በክልሉ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማጠናከርና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ዘርፈ ብዙ ስራዎች ይከናወናሉ፡፡

በተለያዩ የግብርና ሥራዎች የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ ጸሃይ ወራሳን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ እና ወላይቴ ቢቶን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል፡፡

በማቱሳላ ማቴዎስ

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!