የሀገር ውስጥ ዜና

ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

By Amele Demsew

August 19, 2023

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የተያዙት እቃዎች 112 ነጥብ 8 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ የብር ጌጣጌጥ፣ መድሃኒት፣ ሞባይል መለዋወጫ እና የተዘጋጁ ልብሶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እቃዎቹ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ መንገደኞች ላይ በተለይ በዝቅተኛ የሥጋት ደረጃ በሚስተናገዱ መንገደኞች እና ይዘዋቸው በሚገቡ ሻንጣዎች ላይ በተደረገ ጥብቅ የቁጥጥር ስራ ነው የተያዙት ፡፡

በኮንትሮባንድ ዝውውሩ ተሳታፊ የሆኑ ኮንትሮባንዲስቶች፣ ደላሎች እና ሌሎች አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!