የሀገር ውስጥ ዜና

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

By Amele Demsew

August 18, 2023

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመከባበር እና ለጋራ እድገት የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ” መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ትብብራችንን እንቀጥላለንም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።