Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በትግራይ ክልል ቱሪዝምን ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የቱሪዝም አቅምን ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊና ሌሎች የሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች በመቀሌ ከተማ የሚገኘውን የአጼ ዮሐንስ ቤተ መንግስት ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር ተገናኝተው በክልሉ የቱሪዝም ዘርፍን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በውይይታቸውም÷ በክልሉ የቱሪዝም፣ የቅርስ እና ፓርኮች ሀብቶች ልማት፣ ፕሮሞሽን አሁናዊ ሁኔታ እንዲሁም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ መምከራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version