አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ በደረሰ የባቡር አደጋ የ15 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተነገረ።
በደቡብ ምዕራብ ህንድ የእቃ ጫኝ ባቡር ላይ በደረሰው አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ 2 ሰዎች መቁሰላቸውም ነው የተነገረው።
አደጋው የደረሰባቸው ሰዎች በጃልያ አካባቢ በሚገኝ ብረት ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩ ስደተኞች ሲሆኑ ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ነው አደጋው የደረሰባቸው።
ህንድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የእንቅስቃሴ ገደብ ብትጥልም በሚሊየን የሚቆጠሩ ስደተኛ ሰራተኞች መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ከቤት እንደሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ምንጭ፡-ሲ ጂ ቲ ኤን