Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰት ብሩታ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አደርገውላቸዋል ።

አምባሳደር ብርቱካን የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version