Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

9ኛው የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠነኛው የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን ፎረም “ጠንካራ ዲፕሎማሲና ተግባቦት ለዘላቂ የውሃ ሀብት ልማት” በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር/ኢ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የውሃ ሀብቶቿን እንድትጠቀም በዲፕሎማሲውና በተግባቦት ቅንጅታዊ ስራ መሰራት አለበት።

“ስራዎቻችን በሳይንስና በምርምር የተደገፉ ባለመሆናቸው ባለፉት አመታት የውሃ ሀብታችንን እንዳንጠቀም ጫና ፈጥሯል” ነው ያሉት።

ባለፉት አመታት ያሉት ክፍተቶች መጠናታቸውን እና በቀጣይ ውጤታማ መሆን የሚያስችሉ ስራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ የምርምር ተቋማት፣ ሚዲያዎችና ሌሎችም በቅንጅት መስራትን ትኩረት እንዲያደርጉም ሚኒስትሩ አሰገንዝበዋል፡፡

በፎረሙ የተለያዩ የዘርፉ ባለሙያዎች የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ሌሎች አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በመድረኩ ሚኒስቴሩ ስራዎቹን በምርምር የተደገፈ ለማድረግና በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከ5 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የፈረሙት አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ጅማ እና አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

ስምምነቱን ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር/ኢ/ር) እና የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዚዳንቶችና ተወካዮች ፈርመውታል።

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version