የሀገር ውስጥ ዜና

ርዋንዳ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ትሰራለች – አምባሳደር ቻርለስ ካራንባ

By ዮሐንስ ደርበው

August 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ርዋንዳ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እንደምትሰራ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ቻርለስ ካራንባ ገለጹ።

አምባሳደር ቻርለስ የሹመት ደብዳቤቸውን ቅጂ ዛሬ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕሮቶኮል ዋና ሹም አቶ መላኩ በዳዳ አቅርበዋል።

አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ለርዋንዳ ሰላም ቁልፍ ሚና መጫወቷን ገልጸው÷ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ 2012 ትብብራቸውን ለማጠናከር፣ ስትራቴጂካዊ ትብብር ለመፍጠር እና ቋሚ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!